ድምፃዊት ነፃነት ሱልጣን ሩሲያ በሚካሄደው ”ኢንተርቪዥን” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ትወክላለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱድምፃዊት ነፃነት ሱልጣን ሩሲያ በሚካሄደው ”ኢንተርቪዥን” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ትወክላለች
ድምፃዊት ነፃነት ሱልጣን ሩሲያ በሚካሄደው ”ኢንተርቪዥን” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ትወክላለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.09.2025
ሰብስክራይብ

ድምፃዊት ነፃነት ሱልጣን ሩሲያ በሚካሄደው ”ኢንተርቪዥን” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ትወክላለች

"ነፃነት ባሕል እና ዘመናዊውን በማጣመር ኃይለኛ ድምፅ እና ደማቅ የመድረክ አቀራረብን በሥራዎቿ አሳይታለች፡፡ ዘፈኖቿ፣ ዜማና ግጥሞቿ በዘመናዊ ቃና የኢትዮጵያን ሕዝቦች ያንፀባርቃሉ" ሲል አወዳዳሪው በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ድምፃዊቷ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ አድናቆትን አትርፋለች። ነፃነት በሙያዊ ብቃቷ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ላበረከተችው አስተዋፅዖ ሶስት ታላላቅ ሽልማቶችን እንዳገኘች የውድድሩ አዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል ገልጿል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የ2025 "ኢንተርቪዥን" ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር በሞስኮ እና በሞስኮ ክልል እንዲካሄድ አውጀዋል። ውድድሩ መስከረም 10፣ 2018 ዓ.ም በሞስኮ ይካሄዳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0