የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፓን አፍሪካኒዝም ሰንደቅ ተሸካሚ ነው - የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ የፓን አፍሪካኒዝም ሰንደቅ ተሸካሚ ነው - የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፓን አፍሪካኒዝም ሰንደቅ ተሸካሚ ነው - የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.09.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፓን አፍሪካኒዝም ሰንደቅ ተሸካሚ ነው - የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር

ሞሀሙድ አሊ ዩሱፍ ይህን ያሉት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

አየር መንገዱ የኅብረቱን ሥራዎች በመደገፍ እና የአጀንዳ 2063 ራዕይን እውን ለማድረግ የሚጫወተውን ሚና አድንቀዋል፡፡

አየር መንገዱ ለአህጉሪቱ የጥምረት አጀንዳ ከኅብረቱ ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ሥራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፦

አፍሪካን ከዓለም ጋር በማገናኘት፣

አፍሪካውያን ወጣቶችን በአቪዬሸን ዘርፍ በማሠልጠን፣

ለብሔራዊ አየር መንገዶች ድጋፍ በማድረግ፣

የሰላም ፈንድን ጨምሮ ለኅብረቱ ተነሳሽነቶች  አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0