የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ኃይል ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትን ቶንጋ ከተማ ተቆጣጠረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ኃይል ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትን ቶንጋ ከተማ ተቆጣጠረ
የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ኃይል ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትን ቶንጋ ከተማ ተቆጣጠረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.09.2025
ሰብስክራይብ

የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ኃይል ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትን ቶንጋ ከተማ ተቆጣጠረ

በላይኛው ናይል የምትገኘውን ከተማ ከተቃዋሚው የሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ ነፃ አድርጓል። የፓኚካንግ ካውንቲ መቀመጫ የሆነችው ከተማዋ የውጊያ ማዕከል ሆና ቆይታለች ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የመንግሥት ወታደራዊ አዛዦች ኦፕሬሽኑ በጀልባ እና በአየር ድብደባ እንደተፈፀመ ሲገልፁ፤ ተቃዋሚ ኃይሎች በጥይት እጥረት አካባቢውን መልቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ጀነራል ኮንግ ዞው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ያለ ምንም መሣሪያ ወደ አከባቢያቸው እንዲመለሱ አሳስበዋል፡፡

ወታደራዊ ባለሥልጣናት ቶንጋ የትራንስፖርት ግንኙነት ለማስቀጠል ቁልፍ እንደሆነች አንስተዋል፡፡

"ከዛሬ ጀምሮ መንገዶች ይከፈታሉ፡፡... እኛ እዚህ ያለነው የአከባቢውን ደህንነት ለመጠበቅና ትራንስፖርት ክፍት መሆኑን ለማረጋገጥ ነው" ሲሉ ሜጀር ጀነራል ፓሮሚ አንጉኢ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም የተቃዋሚው የሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ ቃለ አቀባይ ኮሎኔል ላም ፖል ጋብርዔል፤ የተባለውን በማጣጣል የእግረኛ ጦር ክፍላቸው ጥቃቱን መቀልበስ ችሏል ብለዋል፡፡

ግጭቱ የተለያዩ ኃይሎችን ወደ አንድ ለማመጣትና ምርጫ ለማድረግ በ2018 የተደረሰውን ስምምነት ውጤት አልባነት ያሳየ እንደሆነ ይነሳል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0