ለምግብ ዋስትናም ሆነ ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት ማዳበሪያ ማምረት መቻል በእጅጉ አስፈላጊ ነው - አወቀ አብርሃም (ዶ/ር)

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለምግብ ዋስትናም ሆነ ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት ማዳበሪያ ማምረት መቻል በእጅጉ አስፈላጊ ነው - አወቀ አብርሃም (ዶ/ር)
ለምግብ ዋስትናም ሆነ ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት ማዳበሪያ ማምረት መቻል በእጅጉ አስፈላጊ ነው - አወቀ አብርሃም (ዶ/ር) - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.09.2025
ሰብስክራይብ

ለምግብ ዋስትናም ሆነ ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት ማዳበሪያ ማምረት መቻል በእጅጉ አስፈላጊ ነው - አወቀ አብርሃም (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት ከናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ከስምምነት ደርሳለች፡፡

በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ተቋም የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የአየር ንብረት መቋቋም ዳይሬክተር አወቀ አብርሃም (ዶ/ር) የተደረሰው ስምምነት ለአርሶ አደሮች፣ በጥቅሉ ለሀገሪቱ ብዙ አበርክቶ ያለው ነው ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

የደህነንት ጉዳዮችና አሁናዊ የዓለም ገበያ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የማዳበሪያ ምርት እየፈተኑት ስለሚገኝ የፋብሪካው ግንባታ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

“አፈራችን የንጥረ ነገር እጥረት አለበት፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ አፈር ውስጥ የናይትሮጅን ንጥረ ነገር እጥረት አለ፡፡...ይህ ፋብሪካ የዩሪያ ማዳበሪያ ነው የሚያመርተው። አጠቃላይ ምርታማነትን ይጨምራል፡፡ ይህ ለምግብ ዋስትናችን ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0