ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያስቀመጠችው የገቢ መጠን መሳካት የሚችል ነው - ከፍተኛ ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያስቀመጠችው የገቢ መጠን መሳካት የሚችል ነው - ከፍተኛ ተመራማሪ
ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያስቀመጠችው የገቢ መጠን መሳካት የሚችል ነው - ከፍተኛ ተመራማሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያስቀመጠችው የገቢ መጠን መሳካት የሚችል ነው - ከፍተኛ ተመራማሪ

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ የወጪ ንግድ ገቢን 9.4 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ መታቀዱን የ2018 በጀት ዓመት እቅድን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ገልፀዋል፡፡

ይህ እቅድ ካለው ተጨባጭ ውጤት አንፃር ማሳከት እንደሚቻል በፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ጀማል መሀመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

አዲስ ምርት ገበያውን ባይቀላቀልም በውጪ ንግድ ምርቶች ላይ መስፋፋትና የኢንቭስትመንት መጎልበት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት አቅም ይሆናል ብለዋል፡፡

“እውነት ለመናገር ከ10 ቢሊዮን በታች ተጨባጭ ነው። ባለፈው ዓመት ስምንት [ቢሊዮን] ማሳካት ከተቻለ ብዙ የሚከብድ አይደለም።...ባለፈው ዓመት አንዱ ትልቅ ለውጥ ያመጣው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ነው” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከወጪ ንግድ ከ8.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ  ማግኘቷ የሚታወስ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0