“ኢትዮጵያን ሀገር በቀል የመድኃኒት ሐብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ወጥ የአጠቃቀም መለኪያ ማዘጋጀት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል”

ሰብስክራይብ

“ኢትዮጵያን ሀገር በቀል የመድኃኒት ሐብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ወጥ የአጠቃቀም መለኪያ ማዘጋጀት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል”

በሀገሪቱ ለዘመናት የፈውስ ምንጭ ሆነው ያገለገሉ ጥንታዊ የዕፅዋት መድኃኒቶች መኖራቸውን ያወሱት የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ፤ ይህ ሐብት የጤና ዘርፉን የመደገፍ የላቀ አቅም እንዳለው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

"እንደ ሕንድ እና ቻይና ባሉ ሀገራት የዕፅዋት ህክምናው ከዘመናዊው ጋር እኩል የሚባል የአገልግሎት ድርሻ አለው። ኢትዮጵያ ውስጥም ለባሕላዊ መድኃኒቶች ትክክለኛ የመጠን እና የአጠቃቀም መለኪያ በማዘጋጀት በስፋት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ ይገባል" ብለዋል።

ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ሀገር በቀል የመድኃኒት ዕውቀቶችን ለትውልዱ ለማስተላለፍ ሊሠሩ ይገባል ያሏቸውን ሐሳቦችም አካፍለውናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0