የገበያ ትስስር ለአፍሪካ የሞት እና ህይወት ጉዳይ ነው ሲሉ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት አሳሰቡ
19:19 02.09.2025 (የተሻሻለ: 19:24 02.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የገበያ ትስስር ለአፍሪካ የሞት እና ህይወት ጉዳይ ነው ሲሉ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት አሳሰቡ
“ያለ ግዙፍ ገበያ፣ ማደግ አይቻልም” ሲሉ ፕሬዝዳንት ዩሪ ሙሴቪኒ የሀገሪቱ ልማት ባንክ ባሰናዳው የኡጋንዳ የፋይናንስ ልማት ጉባዔ ላይ ተናግረዋል፡፡
ትክክለኛ ልማት ለማምጣት እና ወደ አንድ የገበያ ስርዓት ለመግባት የአፍሪካ ሀገራት ከንግግር ባለፈ ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል፦
🟠 በአመራር ውስጥ ራዕይንና ታማኝነትን ማሳደግ፣
🟠 ጥገኛ ያልሆነ ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለትን መፍጠር፣
🟠 በሀገር ውስጥ የማይቀነባበር የሀብት ብዝበዛን ማስቆም፣
🟠 እንደ ኡጋንዳ ልማት ባንክ ያሉ በትርፍ የሚመሩ ሳይሆን ለምርታማነት ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትን መገንባት፡፡
“አንድ ኪሎ ቡና አምርተህ 2.5 ዶላር ታገኛለህ፡፡ ሌላው ሰው ወደ ኔስካፌ ለውጦ በ40 ዶላር ይሸጠዋል፡፡ ማነው ረጂው? አንተ ነህ ረጂው፤ ግን ይህን አታውቀውም” ሲሉም ቁጭታቸውን ገልፀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/