ኢትዮጵያ ካካዋን በሰፊው ለማምረት ከፍተኛ ተፈጥሯዊ አቅም አላት - ከፍተኛ የግብርና ተመራማሪ
18:22 02.09.2025 (የተሻሻለ: 18:24 02.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ካካዋን በሰፊው ለማምረት ከፍተኛ ተፈጥሯዊ አቅም አላት - ከፍተኛ የግብርና ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ካካዋን በሰፊው ለማምረት ከፍተኛ ተፈጥሯዊ አቅም አላት - ከፍተኛ የግብርና ተመራማሪ
ሀገሪቱ ለተለያዩ የካካዋ ዝርያዎች ምቹ የሆኑ ዝቅተኛ እና ሞቃታማ እንዲሁም መካከለኛ የሚባል የአየር ጸባይ ሁኔታን እንደታደለች የተናገሩት፤ በቴፒ የግብርና ምርምር ማዕከል የቅመማ ቅመም እና የካካዋ ሰብሎች ከፍተኛ ተመራማሪው አቡኪያ ጌቱ ናቸው፡፡
የካካዋ ምርት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ወደ ንግድ ስርዓቱ እንዲገባ መደረጉን የገለፁት ባለሙያው፤ ሰብሉን በዘላቂነት ለማምረት የተከናወኑ ተግባራትን ዘርዝረዋል፦
◻ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር እንስቲትዩት የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በካካዋ ምርት ዙሪያ ምርምሮችን አከናውኗል።
◻ ሰብሉ የኢትዮጵያ ሥነ-ምህዳሮች ይላመዳል ወይ የሚለውን የመለየት ሥራ ተሠርቷል፡፡
◻ በምርት ላይ የሚገኘው ዝርያ ከዓለም አቅፍ መመዘኛ መስፈርቶች አንጻር ምርታማነቱ ምን ያህል ነው የሚለው ተፈትሿል፡፡
◻ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን ይቻል ዘንድ በኢትዮጵያ የተመዘገበው ዝርያ የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ያሟላል ወይ በሚለው ዙሪያ ሰፊ ምርምር ተደርጓል፡፡
“ካካዋ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ምርት በመሆኑ እና ቡና ላይ ተንጠልጥሎ የቆየውን የወጪ ምርት ንግድ ለማስፋት እና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የጎላ ድርሻ ስለሚኖረው የባለድርሻ አካላት ትብብር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ባለሃብቶች፣ መንግሥት እና ሌሎችም ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የፖሊሲ፣ የበሽታ ክትትል እና ቁጥጥር ስርዓት፣ ተስማሚ ዘረመሎችን የማከማቸት እና ለተጠቃሚዎች የማሰራጨት እና ካካዋን ወደ ስትራቴጂካዊ ምርት የማሳደግ ተግባራት በቅንጅት ሊያከናወኑ ይገባቸዋል" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X