ኢትዮጵያ በ2018 ከ1 ሺህ 250 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ ለማከናወን አቅዳለች
14:32 02.09.2025 (የተሻሻለ: 14:34 02.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ2018 ከ1 ሺህ 250 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ ለማከናወን አቅዳለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ2018 ከ1 ሺህ 250 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ ለማከናወን አቅዳለች
ሀገሪቱ በ2017 በጀት ዓመት 1 ሺህ 48 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ እና ከባድ ጥገና እንዳከናወነች የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
እንደ አስተዳደሩ ከሆነ በ2018 ዓ.ም፦
◻ 20 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶችን ማጠናከር፣
◻ 285 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ደረጃን ማሻሻል፣
◻ 816.47 ኪሎ ሜትር የአዲስ መንገዶች እና የፍጥነት መንገድ ግንባታ፣
◻ 134.4 ኪሎ ሜትር ከባድ የመንገዶች ጥገና ለማከናወን እቅድ ተይዟል፡፡
የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 175 ሺህ ኪሎ ሜትር እንደደረሰ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2017 ዓ.ም የመጨረሻ የፓርላማ የጥያቄ እና መልስ መርሃ-ግብር ላይ ገልፀው ነበር፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X