ሩስያ እና ኔፓል "በመካከላቸው ምንም አይነት ችግር ኖሮ አያውቅም" - ፑቲን
20:49 01.09.2025 (የተሻሻለ: 14:14 02.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩስያ እና ኔፓል "በመካከላቸው ምንም አይነት ችግር ኖሮ አያውቅም" - ፑቲን
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኔፓል አቻቸው ሻርማ ኦሊ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡
ከሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባዔ ጎን ለጎን የተገናኙት መሪዎቹ ሁለትዮሽ ግንኙንታችውን በሚያጠናክሩብት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡
“በዓለም አቀፍ አጀንዳ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ አቋማችን በጣም ተቅራርቦ መስራት አልያም ሙሉ ለሙሉ በአንድ መሰለፍ ነው፡፡” ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦
ትብብርን ማስፋት፦ በአስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ትብብርን ማጠናከርና ማስፋት የሚቻልባቸውን መንገዶች ለማጤን ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
ኔፓልን ስለመጎብኘት፦ ፑቲን የጠቅላይ ሚኒስትር ጥያቄን ተቀብለውታል፡፡ ‘ ሃሳብህን ተቀብዬ፣ ሀገራቹን ለመጎብኘት አስባለሁ፡፡ እናም በማንኛውም ምቹ ጊዜ እርሶን በሩስያ ውስጥ ለማግኘት ደስተኞች ነን”፡፡
ሰብአዊ ድጋፍ ትኩረት፦ ሩስያ የኔፓል ተማሪዎች በሩስያ ለመማር ፍላጎት ያላቸውን ለማስተናገድና በትምህርት እና ባህል ከኔፓል ጋር ያለውን ትብብር ታስቀጥላልች፡፡
ታሪካዊ ግኑኝነቶች፦ በ1956 የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በቀጣይ ዓመት 70ኛ ዓመቱን ይይዛል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X