- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

ከጎጂ ተክልነት ወደ ግንባታ መሣሪያ ግብዓትነት የተለወጠው የወያኔ ዛፍ ወይም 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ'

ከጎጂ ተክልነት ወደ ግንባታ መሣሪያ ግብዓትነት የተለወጠው የወያኔ ዛፍ ወይም 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ'
ሰብስክራይብ
“ሀሳቤ ለሞቃታማ ሥፍራዎች ተስማሚ ጥሩ የግንባታ መሣሪያ ማምራት ነበር።  ስለዚህ ዋናው ሀሳቤ ከሄምፕክሪት ግንባታ ነበር የመነጨው። ከዛ ነበር ቴክኖሎጂውን የቀዳሁት። ፕሮስክሪት ወደተባለው የራሳችን ምርት ነበር የቴጂክኖሎጂ ሽግግር የተደረገው” ሲል ሲቪል መሃንዲሱ ሱራፌል በላይ ተናግሯል።
'ጁሊፍሎራ' በኢትዮጵያ በረባዳማ ሥፍራዎች ወይም በቆላማ አካባቢዎች የብዝሃ ህይወትን የሚያዛንፍ የአርሶ አደርና አርብቶ አደሩን ህይወት እየጎዳ ያለ መጥፍ ዕፅ ነው። ይህን ተክል ለማስወገድ ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። በዚህ ረገድ የሶቨርኒቲ ሶርስስ አቅራቢ በተለምዶ 'የወያኔ ዛፍ' ተብሎ የሚጠራዉን 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ' ን ከጎጂ ተክልነት ወደ ግንባታ መሣሪያ ግብዓትነት የለወጠው የሲቪል ምህንድስና ባለሙያው ሱራፌል በላይን በመጋበዝ ጥልቅ ወይይት አከናውኗል።
የፀሐይ እና ታዳሽ ኃይል በተመለከተ ከኢትዮጵያ የፀሐይ ሃይል ልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ የምሥራች ሲሳይ ጋር የተደረገው አጭር ቆይታም የፕሮግራሙ ሌላኛው አካል ነው።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsAfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0