የሻንጋይ ትብብር ድርጀት የበለጠ ፍትሐዊ የዓለም አቀፍ የአስተዳደር ሥርዓት በመቅረጽ ሂደት መሪ መሆን ይችላል - ፑቲን
16:43 01.09.2025 (የተሻሻለ: 14:14 02.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሻንጋይ ትብብር ድርጀት የበለጠ ፍትሐዊ የዓለም አቀፍ የአስተዳደር ሥርዓት በመቅረጽ ሂደት መሪ መሆን ይችላል - ፑቲን

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሻንጋይ ትብብር ድርጀት የበለጠ ፍትሐዊ የዓለም አቀፍ የአስተዳደር ሥርዓት በመቅረጽ ሂደት መሪ መሆን ይችላል - ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዝዳንት በሻንጋይ ትብብር ድርጀት ጉባኤ ስብሰባ ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
ከሻንጋይ ትብብር ድርጀት ጋር ለመተባበር የሚጥሩት ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ የዓለም ማኅበረሰብ ለድርጅቱ ያለው ከልብ የመነጨ ፍላጎት እና ትኩረት እያደገ ነው።
የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ችግሮች ቢኖሩም፣ የድርጅቱ ሀገራት የጋራ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ከዓለም አማካይ በበለጠ ፍጥነት እያደገ ነው።
ባሕላዊ እሴቶችን ወደ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ለመመለስ ጊዜው ደርሷል::
ሩሲያ በዓለም አቀፍ አስተዳደር ላይ የሺን ተነሳሽነት ትደግፋለች እንዲሁም የቻይናን ምክረ ሐሳቦች በተጨባጭ ማጤን ለመጀመር ፍላጎት አላት፡፡
በአሁኑ ጊዜ አስር ያህል ሀገራት የሻንጋይ ትብብር ድርጅትን በተለያዩ ቅርጾች ለመቀላቀል የቀረቡ ማመልከቻዎች እየተጤኑ ነው፡፡
ዓለም አቀፋዊ፣ ባሕላዊ እና መንፈሳዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ በሩሲያ የሚካሄደው የኢንተርቪዥን የሙዚቃ ውድድር ከድርጅቱ ሀገራት ከፍተኛ ፍላጎት አነሳስቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X