ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ፑቲን ቱርክን እንዲጎበኙ ግብዣ አቀረቡ
15:23 01.09.2025 (የተሻሻለ: 14:14 02.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ፑቲን ቱርክን እንዲጎበኙ ግብዣ አቀረቡ
ፕሬዝዳንት ፑቲን ከሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ጎን ለጎን ከቱርክ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል።
በዩክሬን ሰላም ማስፈን ሂደት ላይ ቱርክ ላላት አስተዋፅኦ ሩስያ ክብር አላት ሲሉም ፑቲን ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በሂደቱ ላይ ተሳትፎዋ እንዲቀጥልም ፑቲን ጠይቀዋል።
ኤርዶዋን በበኩላቸው ፑቲን ቱርክን ይጎበኛሉ ብለው እንደሚጠብቁ በውይይታቸው ወቅት ተናግረዋል። በባለፈው ዓመት ለሦስተኛ ጊዜ የቀረበላቸው ተመሳሳይ የጉብኝት ጥያቄ ነው፡፡
ስብሰባው በቲያንጂን የፑቲን መኖሪያ ቤት ተካሂዷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X