ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 9 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ግብ አስቀመጠች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 9 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ግብ አስቀመጠች
ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 9 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ግብ አስቀመጠች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ  9 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ግብ አስቀመጠች

የአዲሱ በጀት ዓመት እቅድን ያስታወቁት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ፣ ባለፉት ግዜያት ከተገኙ ውጤቶች በመነሳት በቀጣይ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የተቀመጡ ግቦችን አብራርተዋል።

ሚኒስትሩ የጠቀሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተገኘው የ8 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ የ13.25 በመቶ ጭማሪ ታቅዷል።

ኢትዮጵያ በመጪው መስከረም ወር ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነጻ ንግድ ቀጣና ውስጥ ንግድ ለማስጀምር ዝግጅት ላይ ትገኛለች።

የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል ከ20 በላይ ሀገራት ጋር ንግግሮች እየተካሄዱ ይገኛል፡፡

ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ባንክ ያደረገው የወርቅ ሽያጭ የፖሊሲ ማሻሻያ እና በቡና ምርት የተገኘው ገቢ የወጪ ንግዱን ገቢ ማሳደጉንም ተናግረዋል፡፡

አዲሱ እቅድ የሀገሪቱ የወጪ ንግድ ሥርዓት በተወሰኑ ምርቶች ላይ መሠረት ባደረገበት እና ኢኮኖሚው ለዓለም ተቀያያሪ ገበያ ተጋላጭ በሆነበት ወቅት መቀመጡ ፈታኝ እንደሚያደርገው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0