የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ከፍታውንና የሀገር ውስጥ የበረራ አገልግሎቱን አጠናክሮ ይቀጥላል - ሌተናል ጀነራል ይልማ
12:27 01.09.2025 (የተሻሻለ: 12:34 01.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ከፍታውንና የሀገር ውስጥ የበረራ አገልግሎቱን አጠናክሮ ይቀጥላል - ሌተናል ጀነራል ይልማ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ከፍታውንና የሀገር ውስጥ የበረራ አገልግሎቱን አጠናክሮ ይቀጥላል - ሌተናል ጀነራል ይልማ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1 ቢሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ አስመርቆ አገልግሎት አስጀምሯል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ አየር መንገዱ ወደ ያቤሎ በረራ መጀመሩ ለተቋሙ፣ ለያቤሎ እና ለአካባቢው ሕዝብ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል።
ሌተናል ጀነራል ይልማ፣ አየር መንገዱ በሚታወቅበት ከፍታ ለመቀጠል በትኩረት እየሠራ ያለባቸውን ሦስት ስትራቴጂክ ጉዳዮች ጠቅሰዋል፦
አንደኛ፤ ለሀገር፣ ለአፍሪካ እና ለሌላው ዓለም ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የኢትዮጵያውያ ወጣቶች የአቪዬሽን ሥልጠና፣
ሁለተኛ፤ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ማስፋፋት፣
ሦስተኛ፤ አውሮፕላኖቹን ማዘመን እና የአውሮፕላቹን ቁጥር ማሳደግ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው የነገሌ ቦረና፣ ጎሬ መቱ፣ ሚዛን አማንና ደብረማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያዎች ግንባታ በ2018 ተጠናቀው አገልግሎት እንደሚጀምሩ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X