ፑቲን በቲያንጂን የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ስብሰባ የሀገር መሪዎች ምክር ቤት ላይ ንግግር አድርገዋል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፑቲን በቲያንጂን የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ስብሰባ የሀገር መሪዎች ምክር ቤት ላይ ንግግር አድርገዋል
ፑቲን በቲያንጂን የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ስብሰባ የሀገር መሪዎች ምክር ቤት ላይ ንግግር አድርገዋል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.09.2025
ሰብስክራይብ

ፑቲን በቲያንጂን የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ስብሰባ የሀገር መሪዎች ምክር ቤት ላይ ንግግር አድርገዋል

በሩሲያው ፕሬዝዳንት የተነሱ ዐቢይ ነጥቦች

🟠 የዩክሬን ግጭትን በተመለከተ፦

በአላስካ ስብሰባ ወቅት የተደረሰው መግባባት ለዩክሬን ሰላም መንገድ ከፍቷል፡፡

ለዘላቂ እልባት የዩክሬን ቀውስ ዋና መንሣኤ መወገድ አለበት፡፡

የዩክሬን ቀውስ መነሳት የ”ወረራ” ሳይሆን የመፈንቅለ መንግሥት ውጤት ነው፡

ዩክሬንን ወደ ኔቶ የመቀላቀል የምዕራባውያን ሙከራ የዩክሬን ቀውስ አንዱ ምክንያት ነው፡፡

የዩክሬን ቀውስ እልባት በመስጠት ሂደት፣ ሩሲያ ማንም ሀገር የራሱን ደህንነት በሌላ ሀገር ኪሳራ ላይ ማረጋገጥ አይችልም የሚለውን መርህ ታስረግጣለች፡፡

🟠 በሻንጋይ ትብብር ድርጀት ውስጥ ስለሚደረግ ትብብር በተመለከተ፦

በሻንጋይ ትብብር ድርጀት ውስጥ የሚደረግ ምክክር በኢዩኤስያ (በአውሮፓ እና እስያ) ያረጀውን አውሮፓ ማዕከል ያደረገ እና የአውሮፓ-አትላንቲክ ሞዴል የሚተካ አዲስ የደህንነት ሥርዓት መሠረት ለመጣል ያግዛል፡፡

የሻንጋይ ትብብር ድርጀት ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በመፍታት ረገድ ያለማቋረጥ ተጽዕኖውን እያሳደገ ነው፡፡

የሻንጋይ ትብብር ድርጀት ሀገራት መካከል በሚደረግ ንግድ የብሔራዊ መገበያያ ገንዘቦችን በጋራ መገልገል እየጨመረ መጥቷል፡፡

በሻንጋይ ትብብር ድርጀት ያለው የትብብር እድገት ፍጥነት አስደማሚ ነው፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0