የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ‘አዲስ አይነት ዓለም አቀፍ ግንኙነት’ በመገንባት ሂደት ውስጥ ቁልፍ ኃይል ሆኖ መጥቷል ሲሉ ሺ ጂንፒንግ ተናገሩ
10:02 01.09.2025 (የተሻሻለ: 10:04 01.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሻንጋይ ትብብር ድርጅት ‘አዲስ አይነት ዓለም አቀፍ ግንኙነት’ በመገንባት ሂደት ውስጥ ቁልፍ ኃይል ሆኖ መጥቷል ሲሉ ሺ ጂንፒንግ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ‘አዲስ አይነት ዓለም አቀፍ ግንኙነት’ በመገንባት ሂደት ውስጥ ቁልፍ ኃይል ሆኖ መጥቷል ሲሉ ሺ ጂንፒንግ ተናገሩ
ፕሬዝዳንቱ በጉባኤው የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ላይ እንደተናገሩት፣ “የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ከምሥረታው ጀምሮ፣ አንድነትን እና የጋራ መተማመን በማጠናከር፣ ተግባራዊ ትብብር በማጎለበት እንዲሁም በዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች በንቃት ተሳትፎ ያለማቋረጥ ‘የሻንጋይ መንፈስን’ ከፍ አድርጓል፡፡”
ጉባኤውን በቲያንጂን ማዘጋጀት ለሻንጋይ ትብብር ድርጅት ዘላቄ ልማት አዲስ አንቀሳቃሽ ኃይል የሚሰጥ መሆኑ ላይ ያላቸውን መተማመን ገልፀዋል፡፡
ዓለም ከዚህ ቀደም ታይተው የማይታወቁ ለውጦችን እንዲሁም እንደ አለመረጋጋት እና አይገመቴነት በምታይበት በዚህ ወቅት፣ የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስቀጠል የበለጠ ኃላፊነት ይሸከማል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የቻይናው መሪ አክለው፣ የሻንጋይ ትብብር ድርጅት፣ የአባላቱን አንድነት በማጠናከር፣ ደቡባዊ ዓለምን በማብቃት እንዲሁም በጋራ ጥረቶች የሰው ልጅ ሥልጣኔዎችን በማላቅ ታላቅ ስኬት ያሳካል ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X