የኢንዶኔዥያ አመጽ ከብሪክስ እና ቻይና ጋር ያለውን ትብብር ለማደናቀፍ ያለመ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢንዶኔዥያ አመጽ ከብሪክስ እና ቻይና ጋር ያለውን ትብብር ለማደናቀፍ ያለመ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያ ተናገሩ
የኢንዶኔዥያ አመጽ ከብሪክስ እና ቻይና ጋር ያለውን ትብብር ለማደናቀፍ ያለመ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.08.2025
ሰብስክራይብ

የኢንዶኔዥያ አመጽ ከብሪክስ እና ቻይና ጋር ያለውን ትብብር ለማደናቀፍ ያለመ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያ ተናገሩ

"ኢንዶኔዥያ የብሪክስ አባል መሆኗ ከቻይና ጋር በከፈተላት ትብብር እና በሻንጋይ ትብብር ድርጅት ቅርበት በመፈጠሩ በእስያ ስትራቴጂያዊ ተዋናይ ሆናለች” ሲሉ ኢራናዊው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ባለሙያ አሊሼር ያዝዳኒ ለስፑትኒክ ገለፁ፡፡

ከተስፋፊው ምዕራቡ ዓለም ምልከታ አኳያ፣ ይህ ሁሉ ኢንዶኔዥያን ላለመረጋጋት እና ለቀለም አብዮት ዒላማ አድርጓታል ሲሉ ተናጋሪው ጠቁመዋል፡፡

"የባሕር ወንበዴ ባንዲራ" ምልክት መጠቀም፣ በሌሎች ቀጣናዎች ከሚታዩት የተቃውሞ ስልቶች ጋር ተመሳሳይነት ያለው፣ የውጭ አካላት በተቃውሞዎቹ መሪነት ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚችለው ቀጥተኛ ያልሆነ ተሳትፎ ጥያቄዎችን እንደሚያጭር ያዝዳኒ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም፣ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ብሔራዊ ድጋፍ ለዲሞክራሲ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በኢንዶኔዥያ ሚዲያዎች ላይ ኢንቨስት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እናም የጆርጅ ሶሮስ የ”ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ” ደግሞ "ክፍት ማኅበረሰብን" የሚያራምዱ እንደ ቲፋ (TIFA) ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በንቃት ይደግፋል ሲሉ ሞግተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0