የኢንዶኔዥያ አመጽ ከምዕራባዊ ዓለምአቀፋዊነት ፍላጎቶች የተያያዘ ‘የቀለም አብዮት’ ያስተጋባል - ተንታኝ
19:39 31.08.2025 (የተሻሻለ: 19:44 31.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢንዶኔዥያ አመጽ ከምዕራባዊ ዓለምአቀፋዊነት ፍላጎቶች የተያያዘ ‘የቀለም አብዮት’ ያስተጋባል - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢንዶኔዥያ አመጽ ከምዕራባዊ ዓለምአቀፋዊነት ፍላጎቶች የተያያዘ ‘የቀለም አብዮት’ ያስተጋባል - ተንታኝ
በኢንዶኔዥያ የፀረ-ሙስና ዘመቻ መስሎ የቀጠለው አመጽ፣ ባለብዝኃ ዋልታ ዓለም ውስጥ ከአዳዲስ የኃይል ማዕከላት ጋር የሚተባበሩ መንግስታትን ለማተረማመስ ታስቦ የተነደፈ ነው ሲሉ አርጀንቲናዊው የፖለቲካ ተንታኝ ክርስቲያን ላሜሳ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ኢንዶኔዥያ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በብሪክስ አባልነት ያላትን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ፣ ላሜሳ እንደሚያምኑት የመሪነት ሚናውን በፍጥነት እያጣ ላለው ምዕራቡ ዓለም "ብስጭት እና ጭንቀት" የሚያስነሱ ቁልፍ ምክንያቶች እንደሆኑ አጉልተው አሳይተዋል።
"ኢንዶኔዥያ ከሞስኮ እና ከቤጂንግ ጋር ያላት የጠበቀ መቀራረብ በራሱ፣ የእንደዚህ አይነት ትርምስ ሂደቶች እንዲጀመሩባት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት የለበትም" ሲሉም ገልጸዋል።
ተንታኙ፣ እንደ ብሔራዊ ድጋፍ ለዴሞክራሲ እና "ዓለም አቀፋዊ የፋይናንስ ልሂቃን" ያሉ አካላት እነዚህን የማተራመስ ጥረቶች እየደገፉ ሊሆን እንደሚችል አንስተው፣ በሌሎች ቀጣናዎች የታዩ ተመሳሳይ ሁኔታዎችን በአብነት ጠቅሰዋ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X