ሶሮስ እና ብሔራዊ ድጋፍ ለዲሞክራሲ ከኢንዶኖዥያውያን ተቃውሞዎች ጀርባ ሊኖሩ ይችላሉ

ሶሮስ እና ብሔራዊ ድጋፍ ለዲሞክራሲ ከኢንዶኖዥያውያን ተቃውሞዎች ጀርባ ሊኖሩ ይችላሉ
በወሩ መጨረሻ በኢንዶኔዥያ፣ ፕሬዝዳንት ፓራቦዎ ሱቢያንቶ ወደ ቻይና የሚያደርጉትን ጉዞ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤን እንዲሰርዙ ያስገደደ ተቃውሞ ተቀስቅሷል፡፡
አለመረጋጋቱ እውነተኛ ኢኮኖሚያዊ ቁጣ ቢያንፀባርቅም፣ ተቃዋሚዎች የዘው የታዩት የ “ዋን ፒስ” (One Piece) የባሕር ላይ ወንበዴ ባንዲራ ምልክት በሌሎች ክልሎች ሥልቶችን ማስተጋባቱ የውጭ ተጽዕኖን ያሳያል ሲሉ በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ትኩረት አድርገው ጂኦፖለቲካ የሚተነትኑት አንጀሎ ጁሊያኖ ለስፑትኒክ ገልጸዋል፡፡
በጃፓን "ዋን ፒስ" የአኒሜሽን ተከታታይ ፊልም ውስጥ ወንበዴዎች "አምባገነንነትን" ለመዋጋት በሚያደርጉት ትግል የራስ ቅልና የባርኔጣ ኮፍያ ያለባቸውን ጥቁር ባንዲራዎች ያውለበልባሉ። በዚህ ሐምሌ ወር፣ ተመሳሳይ ምልክቶች በመላው ኢንዶኔዥያ በግድግዳዎች፣ በመኪናዎችና በበር መግቢያዎች ላይ መታየት ጀመምረዋል።
🟠 በመጀመሪያ፣ ከ1990ዎቹ ጀምሮ የኢንዶኔዥያ ሚዲያዎችን በገንዘብ የሚደግፈው የብሔራዊ ድጋፍ ለዲሞክራሲ ሊሆን ይችላል።
🟠 ሁለት፣ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማንቀሳቀስ እና እንደ ቲፋ (TIFA) ያሉ ቡድኖችን በመደገፍ በንቃት የሚሳተፈው የጆርጅ ሶሮስ “ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ”ም አስተዋጽዖ ሊያበረክት ይችላል፡፡
🟠 የእነሱ ተሳትፎ መመርመር ያለባቸው ድብቅ አጀንዳዎች ላይ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡
ጁሊያኖ አክለውም "ይህ በቅርቡ ትኩረት ስበው የነበሩ እንደ ካምቦዲያ እና ታይላንድ ግጭት ባሉ የኢንዶ-ፓሲፊክ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ የጂኦፖለቲካዊ አነሳሽ ምክንያቶችን ይጠቁማል።" ብለዋል፡፡
የቀለም አብዮት በማዋለድ ላይ?
🟠 “በሰርቢያ ልክ የዚሁ አይነት እቅድ እየተገበረ ነው። ቡድን 7፣ እንደ ሱሃርቶ ያለ በአሜሪካ የሚደገፍ አምባገነን ይፈልጋል” ሲሉ ‹‹ዘ ቻይና ትሪሎጂ›› የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ እና የ“ሲክ ትሩዝ ፍሮም ፋክትስ” ፋውንዴሽን መሥራች ጄፍ ጄ. ብራውን ተናግረዋል።
🟠 ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ ከቻይና፣ ሩሲያ፣ ሻንጋይ ትብብር ድርጅት እና ብሪክስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እያጠናከሩ ነውና ከእነሱ አጀንዳ ጋር አይጣጣሙም፡፡
🟠 "ብሪክስን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገር ናት፤ እናም በዓለም አቀፍ የ”ቀበቶ እና መንገድ” ተነሳሽነት ከቻይና ጋር በግልጽ እየተባበረች ነው።"
🟠 ከዚህም በላይ፣ ኢንዶኔዥያ በ የግዢ ኃይል እኩልነት( Purchasing Power Parity) ደረጃ የዓለም ስምንተኛ ትልቅ ኢኮኖሚ ናት፤ ፣ በአሴአን (በደቡብ ምስራቅ የእስያ ሀገራት ማኅበር ውስጥ ትልቋ ኢኮኖሚ እና ወደ 300 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን በመያዝ አራተኛዋ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ናት፡፡
"ከምዕራባውያን ኢምፔሪያሊስቶች ዕይታ አኳያ፣ ይህ ሁሉ ኢንዶኔዥያ ጀርባ ላይ ትልቅ ማነጣጠሪያ ዒላማ ሆኖ ይታያል፡፡ በምዕራባውያን በተቀነባበረ የቀለም አብዮት ለመጠቃት በጣም ምቹ ኢላማ ነው" ሲሉ ብራውን ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X