የኢንዶኔዥያውያን ተቃውሞ፤ አሁናዊ መረጃዎች

የኢንዶኔዥያውያን ተቃውሞ፤ አሁናዊ መረጃዎች
ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ በቻይና የ ሻንጋይ ትብብር ድርጀት ጉባኤ ላይ ለመገኘት እና በመስከረም 3 ቀን 2025 የድል ቀን ሰልፍን ለመታደም ከያዙት ቀጠሮ ቀናትን አስቀድሞ ተቃውሞዎች ኢንዶኔዢያን አንቀጥቅጠዋታል፡፡
🟠 ሀገር አቀፍ ተቃውሞው የተነሳው ነሐሴ 25 ቀን 2025 ነው። ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰልፈኞች በጃካርታ የኢንዶኔዢያን ፓርላማ ጥሰው ለመግባት ሲሞክሩ በፀረ-አመጽ ፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ እና ርችቶችን ሲተኩሱ ታይተዋል፡፡
🟠 ከአደራጅ ቡድኖች ውስጥ አንዱ ጌጃያን መማንጊል እንዳስታወቀው፣ በአብዛኛው ከዮግያካርታ የመጡ ተማሪዎቹ ተቃዋሚዎች ፓርላማ አባላት ደሞዛቸውን እንዲቀንሱ ጠይቀዋል፡፡
🟠 የፓርላማ አባላት በወር ከ100 ሚሊዮን ሩፒያ (6 ሺህ 150 ዶላር) በላይ የሚያገኙ እንደሚያገኙ እና ከፍተኛ የቤት አበልን ጨምሮ ከአማካይ ገቢ እጅግ በጣም ከፍ ያለ መሆኑን የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቦ ነበር፡፡
🟠 የኢንዶኔዥያ የሙስና አቃቢ፣ ኢንዶኔዥያን ኢንስቲትዩት እና የኢንዶኔዥያ የበጀት ግልጽነት ፎረምን ጨምሮ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሀገር ውስጥ የፖለቲከኞችን ገቢ ሲኮንኑ ከርመዋል፡፡
🟠 አርብ ዕለት አንድ የሞተር ሳይክል ራይድ ሹፌር በተቃውሞ ሰለፍ ወቅት ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከተገደለ በኋላ አመጹ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
🟠 የኢንዶኔዥያው ፕሬዚዳንት በሀገር አቀፍ ተቃውሞዎቹ ምክንያት ወደ ቻይና ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰርዘዋል፡፡
🟠 ፕራቦዎ ለሕዝቡን ቁጣ እውቅና በመስጠት፣ ለሕግ አውጪዎች የሚሰጠውን አበል እንደሚቀንሱ እና ቅንጡ የውጭ ሀገር ጉዞዎች ላይ እገዳ እንደሚጥሉ ቃል ገብተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X