ኢትዮጵያ ያስተዋወቀቻቸው ብሔራዊ የካንሰር መቆጣጠሪያ ዕቅድ እና ሀገር አቀፍ የካንሰር መረጃ ምዝገባ መረብ
15:41 31.08.2025 (የተሻሻለ: 15:44 31.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ያስተዋወቀቻቸው ብሔራዊ የካንሰር መቆጣጠሪያ ዕቅድ እና ሀገር አቀፍ የካንሰር መረጃ ምዝገባ መረብ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ያስተዋወቀቻቸው ብሔራዊ የካንሰር መቆጣጠሪያ ዕቅድ እና ሀገር አቀፍ የካንሰር መረጃ ምዝገባ መረብ
የጤና ሚኒስቴር የ2025 እስከ 2029 የሚተገበር ብሔራዊ የካንሰር መቆጣጠሪያ ዕቅድን እና የሀገራዊ የካንሰር መረጃ መመዝገቢያ ሥርዓት ዝርጋታ ማስፋፊያ አስጀምሯል።
ℹ የሕዝብ ተኮር የካንሰር መመዝገቢያ ሥርዓት በአዲስ አበባ ብቻ የነበረ ሲሆን አሁን በመቐለ፣ ሐዋሳ፣ ጎንደር፣ ሐረማያ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች አምስት አዳዲስ ማዕከላት መቋቋማቸው እንደ አዲስ እጥፋት ታይቷል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ "ከጥቂት ጊዜ በፊት የሀገራችንን ክብር በሚያሳንስ መልኩ ኢትዮጵያ የራሷን የካንሰር ጫና ለመገመት የዩጋንዳ የካንሰር መረጃ ላይ ትመረኮዝ ነበር፡፡ ዛሬ ግን እነዚህ የካንሰር መመዝገቢያ ማዕከላት በመጀመራቸው የመረጃችን ባለቤት ሆነናል።” ያሉ ሲሆን በቁርጠኝነት እንዲተገበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአዲሱ ዕቅድ እና በማስፋፊያ በተደረገበት የካንሰር መረጃ ምዝገባ ምክንያት ኢትዮጵያ፦
የካንሰር መከላከል እና በጊዜ የማወቅ መረሃ ግብሮችን ማጠናከር፣
የምርመራ፣ የሕክምና እና የማስታገሻ ክብካቤ ተደራሽነትን ማሻሻል፣
ማስረጃን መሠረት ላደረገ ፖሊሲ እና ዕቅድ አስተማማኝ፣ ሕዝብ ላይ የተመሰረተ የካንሰር መረጃ ማመንጨት፣
ለአኅጉራዊ እና ለዓለም አቀፋዊ የካንሰር ክትትል ተጨባጭ አስተዋፅዖ ማድረግ ትችላለች፡፡
ብሔራዊ የካንሰር መቆጣጠሪያ ዕቅድ፣ በጎርጎሮሳውያኑ 2029 የሀገሪቱን የካንሰር ጫናን በመከላከል፣ በቅድመ ምርመራ፣ በሕክምና እና በማስታገሻ ሕክምና በ15 በመቶ ለመቀነስ ግብ አስቀምጧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ያስተዋወቀቻቸው ብሔራዊ የካንሰር መቆጣጠሪያ ዕቅድ እና ሀገር አቀፍ የካንሰር መረጃ ምዝገባ መረብ

© telegram sputnik_ethiopia
/