በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ እንግዶችን የምታስተናብረው አምሳለ ሰው ሮቦት
13:41 31.08.2025 (የተሻሻለ: 13:44 31.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ እንግዶችን የምታስተናብረው አምሳለ ሰው ሮቦት
"ትብብር" ከሚለው የቻይና ቃል ተወስዶ ሥም የተሰጣት “ዢያኦ ሄ” የፈጠራ ረዳት ሩሲያኛ፣ ቻይንኛ እና እንግሊዝኛ በመናገር ለጋዜጠኞች በጣም ጥሩ ድጋፍ ታቀርባለች፡፡
ኃላፊነቶቿ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
ጉባኤውን በተመለከተ የፕሬስ ማዕከል አሠራር መረጃ መስጠት፣
የጉባኤውን ሁነት የጊዜ መርሃ ግብር ማሳወቅ፣
ተግባራዊ መረጃዎችን ማቅረብ፣
መስተጋብራዊነትን ለመጨመር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የንግግር ልውውጥ ማድረግ፡፡
በቻይና ቲያንጂን የሚካሄደው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የሁለት ቀን ጉባኤ ዛሬ ይከፈታል። ድርጅቱ አስር አባል ሀገራትን እና አስራ ስድስት ታዛቢ አልያም አጋር ሀገራትን የሚያሰባስብ ሲሆን፣ ይህም ገሚሱን የዓለምን ሕዝብ እና 23.5 በመቶ የዓለም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ይወክላል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X