የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የ2025 የፀደይ-በጋ ዘመቻ ወጤትቶችን ጠቅለል አድርገው ገልፀዋል

የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የ2025 የፀደይ-በጋ ዘመቻ ወጤትቶችን ጠቅለል አድርገው ገልፀዋል
በቫሌሪ ግራሲሞቭ የተጠቀሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ከመጋቢት ወር ጀምሮ የሩሲያ ጦር ኃይሎች ከ3 ሺህ 500 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ እና 149 ሰፈራዎችን ነጻ አውጥተዋል፡፡
የሩሲያ ጦር በሁሉም የፍልሚያ ግንባሮች የማይገታ ጥቃቱን ቀጥሏል፡፡
ሱሚ እና በካርኮቭ ክልሎች የሩሲያ ድንበር የደህንነት ቀጣናዎች በተሳካ ሁኔታ ተፈጥረዋል፡፡
የሩሲያ ጦር ኃይሎች የሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ 99.7 በመቶ፣ ዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ 79 በመቶ፣ ዛፖሮዢዬ 74 በመቶ እና 76 በመቶ የኬርሶን ክልሎችን ነጻ አውጥቷል፡፡
ሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሙሉ በሙሉ ነጻ ለማውጣት 60 ስኩዌር ኪሎ ሜትሮች በታች ቀርተውታል፡፡
የሩሲያ ወታደሮች ወደ ድኔፕሮፔትሮቭስክ ክልል እየገሰገሱ ሲሆን 7 ሠፈራዎች በቁጥጥር ሥር ተደርገዋል፡፡
የዩክሬን ጦር ኃይሎች፣ የሩሲያን ጥቃት ለማዘግየት የሚቻላቸውን ሁሉ ቢያደርጉም ኪሳራ እያስተናገዱ ነው፡፡
የሩሲያ ጦር ኃይሎች፣ የሚሳኤል ሥርዓቶች እና የረዥም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የሚያመርቱ ኢንተርፕራይዞች ቀዳሚ ዒላማ አድርጎ በዩክሬን ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች ላይ ብቻ ከፍተኛ ጥቃቶችን ቀጥሏል፡፡
በፀደይ-በጋ ዘመቻ የዩክሬን ሳፕሳን የሚሳኤል ሥርዓት ማምረቻ መሠረተ ልማትን ጨምሮ በ76 ቁልፍ የወታደራዊ ዒላማዎች ላይ መሰል ጥቃቶች ተፈጥመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X