"አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የምናበስርበት ይሆናል" - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
16:08 30.08.2025 (የተሻሻለ: 16:14 30.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የምናበስርበት ይሆናል" - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የምናበስርበት ይሆናል" - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
⏩ የኢትዮጵያ የዓለም ድርጅት አባልነት ድርድር ሂደት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ፣ ሂደቱን ለማፍጠን እና በስኬት ለመቋጨት በበጀት ዓመቱ ሁኔታ ቀያሪ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
አምስተኛው የሥራ ላይ ቡድን ስብሰባ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ “የድርጅቱ አባል ሀገራት በኢትዮጵያ ቁርጠኝነት ላይ የነበራቸው ጥርጣሬ ተወግዶ ሰፊ ድጋፍ እና አንድነት ያገኘንበት ነበር” ብለዋል።
አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ የድርጅቱ አባልነት የሚበሰርበት መሆኑን በመጠቆም፣ ስድስተኛው የሥራ ላይ ቡድን ስብሰባ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሚካሄድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X