ከአፈር አስከ ‘ሶፍትዌር’: የኢትዮጵያ ቡና ዲጂታላይዜሽን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከአፈር አስከ ‘ሶፍትዌር’: የኢትዮጵያ ቡና ዲጂታላይዜሽን
ከአፈር አስከ ‘ሶፍትዌር’: የኢትዮጵያ ቡና ዲጂታላይዜሽን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.08.2025
ሰብስክራይብ

ከአፈር አስከ ‘ሶፍትዌር’: የኢትዮጵያ ቡና ዲጂታላይዜሽን

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ከማሳ እስከ ኤክስፖርት ድረስ በጥራት፣ በመጠን እና በሚፈለገው ጊዜ ለዓለም ገበያ ለማድረስ የሚያስችል የዲጂታል አሠራርና ግብይት እየዘረጋ መሆኑን ገለፀ፡፡

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር የቡና ምርት ዓይነት፣ ጥራት እና መጠን ከኋላ ታሪክ ጀምሮ ለማወቅ የተመዘገበ የዲጂታል ምርት ቋት ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመው በዚህም የተረጋገጠ የቡና ምርት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ እየተሠራ ይገኛል ሲሉ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

የቡና ኢንሼቲቭ ተቀርፆ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ምርትና ምርታማነቱ በሁሉም መስፈርት ማደጉን ገልጸው፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 469 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ መላኩንና በ2018 ዓ/ም ደግሞ ከ600 ሺህ ቶን በላይ ለዓለም ገበያ እንደሚቀርብ ጠቁመዋል።

ባለሥልጣኑ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር በክልሉ የቡና ምርት ግብይት ዲጂታል ፕላትፎርም አተገባበር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0