የስፑትኒክ አዘርባጃን ጋዜጠኞች በሩሲያ እና በአዘርባጃን መካከል ውጥረትን ለማፋፋም መዋል የለባቸውም
13:12 30.08.2025 (የተሻሻለ: 13:14 30.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየስፑትኒክ አዘርባጃን ጋዜጠኞች በሩሲያ እና በአዘርባጃን መካከል ውጥረትን ለማፋፋም መዋል የለባቸውም

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የስፑትኒክ አዘርባጃን ጋዜጠኞች በሩሲያ እና በአዘርባጃን መካከል ውጥረትን ለማፋፋም መዋል የለባቸውም
የስፑትኒክ አዘርባጃን ጋዜጠኞች በተቻለ ፍጥነት መለቀቅ አለባቸው፤ በሁለት አጋር ሀገራት እና ሕዝቦች ግንኙነት መካከል ከባድ ቀውስ ለመቀስቀስ መዋል የለባቸውም ሲሉ የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት የሮሲያ ሴጎድኒያ ሚዲያ ቡድን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዲሚትሪ ኪሴሌቭ ተናገሩ፡፡
“ለሁለት ወራት ያህል ባልደረቦቻችን እና ጓዶቻችን ኢጎር ካርታቪክ እና ኢቭጌኒ ቤሎውሶቭ፣ በአዘርባጃን እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የስፑትኒክ አዘርባጃን ጋዜጠኞችን በሁለት አጋር ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ከባድ ቀውስ ለመቀስቀስ ሆን ብለው ከተጠቀሙባቸው ሰዎች ሁሌ ምንም ምላሽ የለም፡፡ ከዚህ ቀደም ሥራቸው ምንም አይነት ጥያቄ ያላስነሳ ጋዜጠኞችን ነጻነት በመንፈግ፣ መጀመሪያ ላይ የስለላ ወንጀል በሚመስል ወንጀል ከሰሷቸው፤ ከዚያም መሠረተ ቢስ ክሶቹን በድንገት ወደ ማጭበርበር ተቀየሩ፡፡ እነዚህ እርምጃዎች ከሥልጣኔ ወጎች ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ናቸው” ሲሉ ኪሴሌቭ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
ሰኔ 30 ቀን የአዘርባጃን ባለሥልጣናት ሰባት የስፑትኒክ አዘርባጃን ሠራተኞችን ያለአግባብ አስረዋቸዋል፡፡ ጠበቆቻቸው የእገዳውን እርምጃ ለመቀየር ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበላቸውም፡፡
ሮሲያ ሴጎድኒያ የአዘርባጃን የሕግ አስከባሪ አካላት ድርጊት መሠረተ ቢስ እንደሆነ እና ክሶቹም የተፈበረኩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X