በዩክሬን ውጤታማ ሰላም ለማምጣት ሩሲያ ካቀረበችው ጋር ተቀራራቢ ነጥቦች ያስፈልጋሉ - አሜሪካዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
11:39 30.08.2025 (የተሻሻለ: 11:44 30.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበዩክሬን ውጤታማ ሰላም ለማምጣት ሩሲያ ካቀረበችው ጋር ተቀራራቢ ነጥቦች ያስፈልጋሉ - አሜሪካዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዩክሬን ውጤታማ ሰላም ለማምጣት ሩሲያ ካቀረበችው ጋር ተቀራራቢ ነጥቦች ያስፈልጋሉ - አሜሪካዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
“ሰላምን ሊያያሳካ የሚችል እልባት በጣም ግልጽ ነው ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ታዋቂው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ልማት ማዕከል ዳይሬክተር ጄፍሪ ሳክስ ለስፑትኒክ ተናገሩ፡፡
ሳክስ ለሰላም ቁልፍ ናቸው ያሏቸውን ነገሮች ጠቅሰዋል፦
ዩክሬን ገለልተኛ መሆን አለባት፡፡
ዩክሬን የኔቶ አባል መሆን የለባትም፡፡
በሁለቱም ወገን የደህንነት ስጋቶች አሉና የደህንነት ዋስትናዎች ለሩሲያ እና ለዩክሬን የጋራ መሆን
ሳክስ የግዛት ስምምነቶች አስፈላጊ ሊሆኑ እንደሚችሉ አጽንኦት ሲሰጡ፣ ግጭቱ ቀደም ብሎ ተፈትቶ ቢሆን ኖሮ ሊወገድ ይችል የነበረ ሁኔታ መሆኑን ጠቅሰው ነው፡፡
“በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አውሮፓውያኑ እና ዘሌንስኪ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አይቀበሉም፤ እኔም እላለሁ ገሚሱ የአሜሪካ የፖለቲካ መደብም አይቀበላቸውም፡፡” ያሉት ባለሙያው ውጤቱን መተንበይ ፈታኝ ሆኖ የሚቀጥልበትን ምክንያት አስምረውበታል፡፡
በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እንዳሉት፣ የዩክሬን ቀውስ እልባት ለመስጠት መፈታት ያለባቸው ሁለቱ ዋና ዋና ጉዳዮች የኪዬቭ የግዛት ሁኔታ እና የደህንነት ዋስትናዎች ናቸው፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X