ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሁለተኛውን ዓመታዊ የንግድ ሳምንት አስጀመሩ
10:53 30.08.2025 (የተሻሻለ: 10:54 30.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሁለተኛውን ዓመታዊ የንግድ ሳምንት አስጀመሩ
አምራቹን እና ሸማቹን በቀጥታ እንደሚያገናኝ ተስፋ የተጣለበት "ኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ 2025" መገናኛ አምቼ አካባቢ በሚገኘው ጥራት መንደር በይፋ ተክፍቷል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው ይህ የንግድ ትርዒት እና ባዛር ከነሐሴ 24 እስከ 29 ቀን 2025 ዓ.ም ይቆያል፡፡
168 የንግድ ተቋማትን ያሰባሰበው ዝግጅቱ ከንግድ ባሻገር፦
የሀገር ውስጥ ምርቶችንም ለማስተዋወቅ፣
የኢትዮጵያ ምርቶችን ጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ፣
የሀገር ውስጥ ምርቶችን የመጠቀም ባሕልን ማዳበር እና
በንግድ ዘርፍ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X