ፋይናንስን እንደ አዲስ ቅኝ ግዛት መሣሪያ መጠቀምን እንቃወማለን - ፑቲን

ፋይናንስን እንደ አዲስ ቅኝ ግዛት መሣሪያ መጠቀምን እንቃወማለን - ፑቲን
ፕሬዝዳንት ፑቲን ለቻይናው ሺንዋ የዜና ወኪል ከሰጡት የጽሑፍ ቃለ መጠይቅ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
🟠 በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከ2021 ወዲህ የሁለትዮሽ ንግድ በ100 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡
🟠 በሩብል እና በዩዋን እየተካሄዱ ያሉት ግብይቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ ሲሆን፣ ይህም በዶላር እና በዩሮ ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነሱን ገልፀዋል፡፡
🟠 ሩሲያ ለቻይና ግንባር ቀደም የኃይል አቅራቢ ሆና መቀጠሏን አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡ ከ100 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ጋዝ በ"ፓወር ኦፍ ሳይቤሪያ" የቧንቧ መስመር በኩል አስቀድሞ ደርሷል፡፡
🟠 ከ51 ሺህ በላይ ቻይናውያን ተማሪዎች በሩሲያ እና 21 ሺህ ሩሲያውያን ተማሪዎች በቻይና መገኘታቸውን ጠቅሰው የባሕል እና የትምህርት ልውውጦች አስፈላጊነትን አስምረውበታል፡፡
🟠 ፑቲን "ናዚዎችን፣ ወታደራዊ ኃይሎችን እና አጋሮቻቸውን ለማወደስ ወይም የሶቪዬት ነጻ አውጪዎችን ሥም ለማጥፋት የሚደረጉ ማናቸውንም ሙከራዎች እናወግዛለን" ብለዋል፡፡
🟠 ሺ ጂንፒንግን "የዓለም ኃያል ኃይል እውነተኛ መሪ፣ ጠንካራ መሻት ያላቸው፣ የስትራቴጂያዊ ራዕይ እና ዓለም አቀፋዊ እይታ ብቃት የተላበሱ ሰው" በማለት አሞካሽተዋቸዋል፡፡
🟠 ሩሲያ እና ቻይና የተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያዎችን እንደሚደግፉ እና ፋይናንስን እንደ አዲስ ቅኝ ግዛት መሣሪያ መጠቀምን እንደሚቃወሙ አረጋግጠው "ለሁሉም የሰው ዘር ጥቅም እድገትን እንሻለን" ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X