ዘሌንስኪ ዩክሬን ድንበሮቿን ማስመለስ እንደማትችል አመኑ

ሰብስክራይብ

ዘሌንስኪ ዩክሬን ድንበሮቿን ማስመለስ እንደማትችል አመኑ

“የግጭቱ መቋጫ ወታደራዊ አልያም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዛሬ ደንበሮቻችንን በኃይል ማስመለስ እንደማይቻለን ተገንዘበናል፡፡ ከጦርነት አንጻር ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ፈጣን እና አነስተኛ ኪሳራዎች ያሉት ነው” ሲሉ በኪዬቭ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል፡፡

ክሬምሊን በዩክሬን ድርድር ዙሪያ ምንም አይነት መሻሻል ባይመለከተም ለእነሱ ክፍት መሆኑን አስታውቋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የድርድሮቹ፣ ውጤት የዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት፣ ናዚያዊነትን ማስወገድ፣ ከማንም ያልረተጣመረች ገለልተኛ እና ኑክሌር ጦር መሣሪያ አልባ ቁመና፣ የግዛት እውነታዎችን እውቅና መስጠት፣ የሩሲያውያን እና የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች መብቶች ጥበቃ እንዲሁም የቀኖናዊቷ ኦርቶዶክሳዊነት ስደት እንዲያበቃ የሚያስችሉ ውጤቶችን ማምጣት እንዳለባቸው ገልጿል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0