“ታሪኮቻችንን በመጻፍ፣ ታሪኮቻችንን እንደገና በመጻፍ እና የራሳችንን ትርክት በአጀንዳ ላይ በማስቀመጥ፣ እነዚህን ትርክቶች በራሳችን ባህላዊ እና ማህበራዊ አመለካከቶች በመቅረጽ የአፍሪካ ሚዲያ እና የመገናኛ ብዙሃን ምሁራን በቅኝ ግዛት ቅርስ ስር የሰደዱትን የምዕራባውያን የጋዜጠኝነት ሞዴሎችን የበላይነት መሞገት ይገባቸዋል።” ፕሮፌሰር ማርጋሬት ጁኮ፣ የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒኬሽን ማህበር (EACA) ፕሬዝዳንት
“ከአፍሪካ የመጡ ጋዜጠኞች በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ላይ ያለውን አድልኦ፣ የተሳሳተ መረጃን እና የውሸት ዘገባን ለመመከት ተባብረው መስራት አለባቸው።” ዮሐንስ ሽፈራው (ፒኤችዲ)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ረዳት ፕሮፌሰር
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ እ.ኤ.አ ከነሐሴ 27–29፣ 2025 በአዲስ አበባ የተካሄደውን 15ኛውን የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒኬሽን ማህበር ኮንፈረንስ እንቃኛለን። ዓለም አቀፍ ሚዲያ ከምዕራባውያን የበላይነት ሞዴል ወደ ብዝሀ ሃይል ቅርጽ እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት፣ የአፍሪካ ድምፆች የራሳቸውን ትርክቶች በመቅረጽ የተሻሻለ ሚና እንዲኖራቸው እየጠየቁ ነው። በአህጉሪቱ ከሚገኙ ታዋቂ ምሁራን እና የሚዲያ ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ በማነጋገር የተሰናዳውን ይህን ፕሮገራም ይከታተሉ።