የፑቲን የቻይና ጉብኝትን በተመለከተ እስካሁን ይፋ የሆኑ መረጃዎች

የፑቲን የቻይና ጉብኝትን በተመለከተ እስካሁን ይፋ የሆኑ መረጃዎች
የሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ቁልፍ ዝርዝሮችን ይፋ አድርገዋል፦
🟠 ፕሬዝዳንት ፑቲን ከነሃሴ 25 አእስከ ነሃሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም፣ በቲያንጂ በሚካሄደው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ እና በቤጂንግ የሚከበረውን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያበቃበት 80 ዓመት በዓል ላይ ለመሳተፍ ቻይናን ይጎበኛሉ፡፡
🟠 በጉብኝታቸው ከሺ ጂንፒንግ፣ ከሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን፣ ከሰርቢያው ፕሬዝዳንት ቩቺቺ፣ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ኢርዶዋን እና ከኡዝቤኪስታን ፕሬዝዳንት ሚርዚዮዬቭ ጋር ይገናኛሉ፡፡
🟠 ሩሲያ እና ቻይና በአሜሪካ ግንኙነቶች እና በዩክሬን ሁኔታ ላይ የሻይ ሠዓትን ጨምሮ በጋራ እና በተናጠል መድረኮች ውይይት ያደርጋሉ፡፡ የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር ቤሉሶቭ የግል ውይይቱ ላይ ይሳተፋሉ፡፡
🟠 ሩሲያ በፑቲን እና በሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን መካከል የሁለትዮሽ ስብሰባ በቻይና የማካሄድ አጋጣሚዎችን እየፈለገች ነው፡፡
🟠 በቤጂንግ በፑቲን እና በአዘርባጃን መሪ አሊዬቭ መካከል የታቀደ ስብሰባ የለም፤ ምንም እንኳን ሁለቱም የ80ኛ ዓመት ዝግጅቶች ላይ የሚታደሙ ቢሆንም፡፡
🟠 ትራምፕ በቤጂን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሁነት ላይ በእንግድነት ከተጋበዙት መካከል አይደሉም፡፡
🟠 ኡሻኮቭ የሩሲያ፣ ቻይና እና የሞንጎሊያ መሪዎች የሦስትዮሽ ስብሰባ በቤጂንግ እንደሚደረግ ይፋ አድርገዋል፡፡
🟠ለቤጂንግ ውይይት የሩሲያ ልዑክ፣ ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን፣ ከአሥር በላይ ሚኒስትሮችን፣ የመንግግሥት ኩባንያዎች ኃላፊዎችን እና ዋና ዋና የንግዱ ዘርፍ ተወካዮች ያካትታል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X