ናይጄሪያ ነባር የነዳጅ ማጣሪያዎችን ለማዘመን እና አዳዲሶችን ለመገንባት 60 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ አቀደች
18:05 29.08.2025 (የተሻሻለ: 18:14 29.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ ነባር የነዳጅ ማጣሪያዎችን ለማዘመን እና አዳዲሶችን ለመገንባት 60 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ አቀደች
ግቡ በአሁኑ አሥር ዓመት መጨረሻ የነዳጅ የማጣራት መጠኗን በመጨመር 50 ሺህ በርሜል በቀን ማድረስ መሆኑን የናይጄሪያ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ባዮ ኦጁላሪን ጠቅሶ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
እንደ እሳቸው ከሆነ ኩባንያው የሚከተሉትን አቅዷል፦
🟠 በናይጄሪያ የነዳጅ ማጣሪያ ሥራ እንዲያንሰራራ ማድረግ፣
🟠 የነዳጅ ምርትን ወደ 3 ሚሊዮን በርሜል በቀን ማሳደግ፣
🟠 በጋዝ ኢንዱስትሪ ውስጥ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት ናቸው፡፡
በአጠቃላይ እቅዶቹ የቀጠሉትን የነዳጅ እና የጋዝ ኢንዱስትሪ ማሻሻያዎች ይመለከታሉ፤ ለዚህ ትግበራ ደግሞ የጋራ ሽርክናዎች በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X