ሳይንቲስቶች ሦስት ግራም ብቻ የምትመዝን አዲስ አጥቢ ዝርያ በኢትዮጵያ አገኙ
17:29 29.08.2025 (የተሻሻለ: 17:34 29.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሳይንቲስቶች ሦስት ግራም ብቻ የምትመዝን አዲስ አጥቢ ዝርያ በኢትዮጵያ አገኙ
በሰሜን ተራሮች ክሩሲዱራ የሚሰኙ አይጥ መሰል የአጥቢ እንሳት ዝርያ ናት የተገኘችው፡፡
ይህች ሚጢጢ አጥቢ በጎርጎሮሳውያኑ 2015 በተመራማሪ ዊልያም ቲ. ስታንሌይ የመጨረሻ የመስክ ሥራቸው ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰብስባለች፡፡ በነሐሴ 20 በጆርናል ኦፍ ቨርተብሬት ባዮሎጂ ላይ በታተመ ጥናት መሠረት፣ አሁን ለሳይንስ አዲስ ዝርያ መሆኗ ተረጋግጧል፡፡
ተመራማሪዎች በሕትመታቸው "ግኝቱ የኢትዮጵያን የበለጸገ ብዝኃ ሕይወት እና የደጋማ አካባቢዎች፣ ምድር ላይ በየትኛውም አካባቢ የማይገኙ አጥቢ እንስሳት መኖሪያ የሆነው የምስራቅ አፍሮሞንቴን መገኛ ነጥብ አካል መሆናቸውን ያጎላል፡፡" ብለዋል፡፡
አይጥ የምትመስለው አጥቢዋ፣ "ሚጢጢ ባለ ሁለት ቀለም" አጥቢ እንስሳ በሚል ትገለጻለች፡፡ ከላይ ጥቁር ቡናማ-ግራጫ ፀጉር እና ከታች ደግሞ ነጣ ያለ ግራጫ ፀጉር፣ ጠፍጣፋ ጭንቅላት እና አጭር ቆም ቆሙ ያሉ ፀጉሮች ያሉት ጭራ አላት።
ጭንቅላቷ እና ሰውነቷ ወደ 2 ኢንች የምትረዝም ተጨማሪ 1.2 ኢንች ጭራ ያላት ናት፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia