የኢትዮ ቴሌኮም እና የሳውዲ ቴሌኮም ስምምነትን ተከትሎ ቴሌብር በሳውዲ አረቢያ አገልግሎት ሊሰጥ ነው
16:09 29.08.2025 (የተሻሻለ: 16:14 29.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮ ቴሌኮም እና የሳውዲ ቴሌኮም ስምምነትን ተከትሎ ቴሌብር በሳውዲ አረቢያ አገልግሎት ሊሰጥ ነው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮ ቴሌኮም እና የሳውዲ ቴሌኮም ስምምነትን ተከትሎ ቴሌብር በሳውዲ አረቢያ አገልግሎት ሊሰጥ ነው
ኢትዮ ቴሌኮም እና የሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያ ትልቁ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት የሆነውን ቴሌብር ወደ ሳውዲ ገበያ ለማስገባት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
በሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ የሴልስ ከርየር እና ሆልሴል ምክትል ፕሬዝዳንት ዚያድ ሃማድ ኤ. አልሃሶን እና የከርየር ሴልስ ዳይሬክተር ባንደር ኤ. አልኮዳይር የተመራ ልዑክ ከኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “ለጋራ ተጠቃሚነት ብዙ ልንተባበርባቸው እና አዳዲስ የዕድገት አማራጮችን ልንፈልግላቸው የምንችላቸው ዘርፎች ያሉ ሲሆን፤ እነዚህም የሀገሮቻችንን ዲጂታል ሽግግር የሚያሳድጉ እና ይበልጥ ሁሉን አቀፍ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትን የሚያፋጥኑ ዕድሎች ናቸው” ብለዋል።
ሁለቱ ኩባንያዎች ከስምምነት ከደረሱባቸው ጉዳዮች ውስጥ፦
▪ሁለቱም ኩባንያዎች የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማሳደግ፣
▪የድንበር ተሻጋሪ የሀዋላ እና የክፍያ ሥነ ምህዳሮችን ለማጠናከር፣
▪ቴሌብር እና ሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ የክፍያ ሥርዓቶችን ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት አድርገዋል።
ውይይቶቱ የዲጂታል መሠረተ ልማት አቅሞችን ለማስፋፋት፣ የጅምላ ንግድ ትብብርን እና የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶች ውህደትን ለማጠናከር ተጨባጭ ስትራቴጂዎችን ለመዳሰስ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X