የሩሲያ ሥነ-ጽሑፍ ውቅያኖስ ነው - ኢትዮጵያዊ ደራሲ
15:22 29.08.2025 (የተሻሻለ: 15:24 29.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ሥነ-ጽሑፍ ውቅያኖስ ነው - ኢትዮጵያዊ ደራሲ
አንጋፋው ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት እና ተርጓሚ ዓለማየሁ ዓሊ፣ የሩሲያ መጻሕፍት ለዓለም ሥነ-ጽሑፍ ባለውለታ መሆናቸውን ይገልጻሉ።
በተለይ የእርሳቸው ትውልድ ከንባብ ጋር ይበልጥ ይተዋወቅ የነበረው በሩሲያ መጻሕፍት መሆኑን የሚያወሱት ደራሲው፣ የሩሲያን ሥነ-ጽሑፍ መውደድ ውዴታ ሳይሆን ዕጣ ፈንታ መሆኑን ያነሳሉ።
"የሩሲያን ሥነ-ጽሑፍ ወደህ ሳይሆን ተገደህ ነው የምትወደው። ከይቅርታ ጋር ሼክስፒርን ከሩሲያን ክላሲክ ጽሑፎች ጋር ሳነጻጽረው የእርሱ (ግጥሞቹ ሲቀሩ) ተረታ ተረት ነው የሚሆንብህ" ይላሉ።
ዓለማየሁ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የሩሲያ ሥነ-ጽሑፍ የደም እና የአጥንት ዋጋ የተከፈለበት መሆኑን አንስተው፣ የሀገሪቱ ደራሲዎቸ በርካታ ዘመን አይሽሬ መጻሕፍትን ማበርከት ስለቻሉበት ምስጢርም አካፍለውናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X