አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ በወርቅ ማውጣት እና በሪል እስቴት ዘርፍ መሠማራት እንደሚፈልጉ ገለፁ
13:47 29.08.2025 (የተሻሻለ: 13:54 29.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ በወርቅ ማውጣት እና በሪል እስቴት ዘርፍ መሠማራት እንደሚፈልጉ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ በወርቅ ማውጣት እና በሪል እስቴት ዘርፍ መሠማራት እንደሚፈልጉ ገለፁ
ዳንጎቴ ግሩፕ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንቱን ከሲሚኒቶ እና ከማዳበሪያ ባሻገር ለማስፋት እየተዘጋጀ ነው፡፡
የአሊኮ ግሩፕ ሊቀመንበር አሊኮ ዳንጎቴ “የወርቅ እድሎችን እያጤንን ነው፡፡ እነዚህ ለእኛ አዲስ ሥራዎች ቢሆኑም እንደ ሥራ ፈጣሪ ኩባንያ እያንዳንዷን ኢንቨስትመንት እንመለከታለን፡፡ በንብረቶች(ልዩ ልዩ ቤቶች) እና አፓርትመንት ሕንጻዎች ግንባታ ውስጥም ልንሰማራ ሁሉ እንችላለን” ሲሉ በጎዴ ከተማ በ2.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስን ፊርማ ወቅት ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ውስጥ አስቀድሞ ጠንካራ መሠረት የጣለው ቡድኑ፣ በከተማ ዕድገት ምክንያት በሪል እስቴት ለመሠማራት አሳማኝ መንገድ እንዳለ ተመልክቷል፡፡
ኩባንያው ወደ ወርቅ ማዕድን ሥራ ለመሰማራት መወጠኑ የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ እያደገ የመጣ ፍላጎት ያንፀባርቃል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X