ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የአቬሽን አጋርነት እያጤኑ ያሉት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት
12:09 29.08.2025 (የተሻሻለ: 12:14 29.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የአቬሽን አጋርነት እያጤኑ ያሉት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር፣ በጁባ ከኢትዮጵያው የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በሚኖራቸው አጋርነት የደቡብ ሱዳንን የአቪዬሽን ዘርፍ ማጠናከርን መማተራቸውን የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በ2023 በሀገራቱ መካከል የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ ሱዳን የሚቋቋመው ብሔራዊ አየር መንገድ 49 በመቶ ድርሻ እንዲይዝ መንገድ ከፍቷል፡፡
የሁለቱ ወገኖች ውይይት፦
የአየር ትራንስፖርት እና የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ማሳደግ፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደቡብ ሱዳን የአቪዬሽን ዘርፍን የሚያሻሽልበትን ሁኔታ፣
በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች እና በቴሌኮሙኒኬሽን የጋራ ልማት፣
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የደቡብ ሱዳን የፋይናንስ ተቋማት ትብብር፣
ደቡብ ሱዳንን፣ ኢትዮጵያን እና ጅቡቲን የሚያገናኝ የንግድና ትራንስፖርት ኮሪደር መፍጠርንም ተመልክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X