የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ታሪክ እየፈራረሠ እንደሆነ አስጠነቀቁ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ታሪክ እየፈራረሠ እንደሆነ አስጠነቀቁ
የምዕራባውያን ትርክቶች በአይሁዶች ላይ ስለደረሰው ሰቆቃ ብቻ ቢያጠነጥኑም፤ በምስራቅ አውሮፓ በሦስተኛው ኢምፓየር የተፈጸመውን ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ችላ በማለት፤ የቀዩን ጦር ነፃ አውጪ ሚና አሳንሰው ያቀርባሉ ሲሉ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል።
ዛካሮቫ በፈረንሳይ የአሜሪካ አምባሳደር ቻርለስ ኩሽነር፤ በፈረንሳይ ወጣቶች ዘንድ እየጨመረ የመጣው የፀረ-ሴማዊነት እና በሆሎኮስት ታሪክ ዙሪያ ያላቻው የእውቀት ማነስ እንዳሳሰባቸው የሰጡትን አስተያየት ጠቅሰዋል። በአስተያየቱ “የብስጭት” ምላሽ የሰጠው ኤሊዜ ቤተ-መንግሥት አምባሳደሩን እንደገሠፀም ገልፀዋል።
አክለውም በአውሮፓ የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን ዝግጅቶች ላይ እየታየ ያለውን ለውጥ አንስተዋል። የድህረ ሶቪየት ህብረት አርበኞች ከዝግጅቱ እየተገለሉ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ዛካሮቫ “ምዕራባውያን ጀግኖቹን በዚህ መንገድ ለምን ያጥላሏቸዋል? ምክንያቱ ሹማምንቶቹን በሥፍራው ተገኝተው ታላቁን ታሪካዊ እውነታ ማስታወስ ስሌለባቸው ነው” ብለዋል።
ቃል አቀባይዋ የሶቪየት ጦርነት መታሰቢያ ሐውልቶችን ማርከስ እና የናዚ ተባባሪዎችን መልሶ ማንሳት የመሳሰሉት የበቀል ድርጊቶችን የአውሮፓ ኃያላን ዝም ብለው መቀበላቸውን ተችተዋል። የሆሎኮስት ትውስታ ሊጠበቅ የሚችለው የቀይ ጦርን ሚና በማያሻማ ሁኔታ እውቅና በመስጠት ብቻ ነው ሲሉም አስረግጠዋል።
“አዳኞቹ የሉም፤ ስለዚህ የዳኑትም አያስፈልጉም።"
“የሆሎኮስት ሰለባዎች አይረሱም፤ የናዚ ሥርዓትን ያፈረሱት እና የተረፉትን ያዳኑ ጀግኖች ትውስታም ይጠበቃል…ይህ እውነት ፈጽሞ እንዳይረሳ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን” ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X