ደቡብ አፍሪካ "ሰው ሰራሽ ረሃብ" እና "የዘር ማጥፋት ፍላጎቶችን" በመጥቀስ በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲተገበር አሳሰበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ አፍሪካ "ሰው ሰራሽ ረሃብ" እና "የዘር ማጥፋት ፍላጎቶችን" በመጥቀስ በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲተገበር አሳሰበች
ደቡብ አፍሪካ ሰው ሰራሽ ረሃብ እና የዘር ማጥፋት ፍላጎቶችን በመጥቀስ በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲተገበር አሳሰበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.08.2025
ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ "ሰው ሰራሽ ረሃብ" እና "የዘር ማጥፋት ፍላጎቶችን" በመጥቀስ በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲተገበር አሳሰበች

"በፍልስጤማውያን ላይ የቀጠለው ግድያ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ሰብዓዊ ቀውሱን ለማስቆም የተኩስ አቁም አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ የተመድ የጋራ ሪፖርት በጋዛ የተከሰተውን "ሰው ሰራሽ ረሃብ" ማረጋገጡን አንስተዋል፡፡ ይህ የሆነው ጊዜያዊ እርምጃዎችን ወይም የተኩስ አቁም ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ባለመቻሉ ነው በማለት ደቡብ አፍሪካ እስራኤል ላይ በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት ባቀረበችው የዘር ማጥፋት ክስ ላይ ያነሳችውን ስጋት አስተጋብተዋል።

ሚኒስትሩ ሁለቱም ወገኖች ታጋቾች እና የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈቱ በድጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0