ቦይንግ የአዲሱን የ777X ምርት የተስማሚነት ምዘና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ማድረግ እንደሚፈልግ አስታወቀ
15:13 28.08.2025 (የተሻሻለ: 15:14 28.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቦይንግ የአዲሱን የ777X ምርት የተስማሚነት ምዘና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ማድረግ እንደሚፈልግ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቦይንግ የአዲሱን የ777X ምርት የተስማሚነት ምዘና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ማድረግ እንደሚፈልግ አስታወቀ
የቦይንግ ኩባንያ ልዑክ ለአዲሱ ምርት ፍተሻ ቅድመ ፈቃድ ለማግኘት ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮሀንስ አበራ ጋር ተወያይቷል።
የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የከፍታ አቀማመጥ የአውሮፕላኑን ብቃት ለመፈተሽ ምቹ እንደሆነ በውይይቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡
እ.አ.አ በ2006 ኤር ባስ ኤ380 የተሰኘውን ሞዴሉን በቦሌ ዓለም አቀፍ ማረፊያ የተስማሚነት ምዘና ማድረጉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውሷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X