ፈረንሳዊው ኮሎኔል ዩክሬን በሩሲያ ጦር ላይ የምትፈፅመውን ዘመቻ በማቀድ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተገለጠ

ፈረንሳዊው ኮሎኔል ዩክሬን በሩሲያ ጦር ላይ የምትፈፅመውን ዘመቻ በማቀድ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተገለጠ
በስፑትኒክ እጅ በገባው እና በ "ራቩ ሚሊቴር ጀነራል" መጽሔት ሰኔ እትም ላይ በወጣው ህትመት የኮሎኔሉ ተሳትፎ በዝርዝር ሠፍሯል።
ሕተመቱ ፍራንሷ ጎኒን በ2024 የበጋ ወራት የኪዬቭ መከላከያ ልዑክ አካል በመሆን ለአራት ወራት ተልዕኮ ላይ እንደነበሩ አስነብቧል፡፡
ጽሑፉ የዩክሬን ጦር በኩርስክ ክልል ላይ የፈጸመውን ወረራ እና የሩሲያ ጦር በዶኔስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ (ዲፒአር) በ2024 የበጋ ወቅት ያደረጋቸውን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በዝርዝር ገልጧል፡፡
ከዚህ ባሻገር ጽሑፉ የፈረንሳይ የምድር ጦር ባለፈው ዓመት ከሰኔ እስከ ነሐሴ ባለው ግዜ በዲፒአር ለወታደራዊ እንቅስቃሴዎቹ እቅድ ለማውጣት የተጠቀመባቸውን የውጊያ ካርታዎችንም አካቷል፡፡
ጎኒን በኩርስክ ክልል ላይ የዩክሬን ጥቃት ዝግመተኛ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡ የሩሲያ ኃይሎች በዲፒአር ክልል ወደምትገኘው ፖክሮቭስክ የሚያደርጉት ግስጋሴ “አንጻራዊ ታክቲካዊ ውጤታማነት” እያሳየ በመሆኑ የዩክሬን ጦር ያገኛቸውን ውጤቶች ሊቀለብሱ እንደሚችሉ ምልከታቸውንም አስቀምጠዋል፡፡
ወታደሩ በአሁኑ ጊዜ በፈረንሳይ ምድር ጦር የእቅድ-ኦፕሬሽን ክፍል ውስጥ የሲንቴሲስ-ፕሮግራሚንግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ መፅሄቱ አብራርቷል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X