በአፍሪካ የቢሊየነሮች ቁጥር በ25 ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ አደገ
20:11 27.08.2025 (የተሻሻለ: 20:14 27.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአፍሪካ የቢሊየነሮች ቁጥር በ25 ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ አደገ
ሄንሌይ ኤንድ ፓርትነርስ የተባለ ተቋም ባወጣው ሪፖርት መሠረት፤ አህጉሪቱ በ2025 መጨረሻ 25 ቢሊየነሮች ይኖሯታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ቁጥር በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ በ65% እንደሚያድግም ተገምቷል፡፡
ይህ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጋር ከነበረው አነስተኛ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር “አስደናቂ” ውጤት እንደሆነ ተገልጿል።
የአህጉሪቱን እያደገ የመጣ ሀብት የሚያሳዩ አንዳንድ መረጃዎችን እነሆ፦
⏺ አፍሪካ የ122 ሺህ ሚሊየነሮችና የ348 ሴንቲ-ሚሊየነሮች መገኛ ነች፡፡
⏺ ደቡብ አፍሪካ 41 ሺህ 100 ሚሊየነሮች ያሏት ሲሆን በዚህም ከአጠቃላይ ቁጥሩ 34% የሚሆነውን ትሸፍናለች፡፡
⏺ ግብጽ (በ14 ሺህ 800 ሚሊየነሮች)፣ ሞሮኮ (በ7 ሺህ 500)፣ ናይጄሪያ (በ7 ሺህ 200) እና ኬንያ (በ6 ሺህ 800) ይከተላሉ፡፡
⏺ የተጠቀሱት ሀገራት ብቻ የአህጉሪቱን 88% ቢሊየነሮች ይሸፍናሉ፡፡
⏺ የባለሀብቶቹ መጨመር በጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት የተደገፈ ነው። የከሰሃራ በታች አፍሪካ ኢኮኖሚ በ2025 በ3.7% እንደሚያድግ ይጠበቃል። ይህም ከአውሮፓ የ0.7% ዕድገት ጋር ሲነፃፀር ትልቅ ነው፡፡
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X