በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዘረመል ማሻሻያ የደረገለት የአሳማ ሳንባ ለሰው ልጅ በተሳካ ሁኔታ ተተከለ
19:57 27.08.2025 (የተሻሻለ: 20:04 27.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዘረመል ማሻሻያ የደረገለት የአሳማ ሳንባ ለሰው ልጅ በተሳካ ሁኔታ ተተከለ
የቻይና ጓንዡ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ቡድን አእምሮው በሞተ ሰው ላይ ቀዶ ጥገናውን በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ ፈር ቀዳጅ ህክምና አስመዝግቧል።
🫁 ንቅለ ተከላው ለዘጠኝ ቀናት ያህል መሥራት መቻሉ፤ ከእንስሳት ወደ ሰዎች ለሚደረግ የአካል ክፍል ዝውውር "xenotransplantation" ህክምና ተስፋ ሰጪ ምዕራፍን ከፍቷል ተብሏል።
በኔቸር ሜዲሲን ላይ የታተመው ውጤት በንቅለ ተከላ የተተካው ሳንባ ሁለት ጊዜ የበሽታ መከላከያ ምላሽ ምልክቶችንም ቢያሳይም በህክምና ማስተካከያዎች በተሳካ ሁኔታ መፍትሄ ማግኘት ችሏል።
🫁 ሙከራው በቤተሰቡ ጥያቄ የቆመ ቢሆንም ወደፊት በተለያዩ ፍጥረቶች መካከል ለሚደረጉ የንቅለ ተከላ ምርምሮች ጠቃሚ የሆኑ አስፈላጊ መረጃዎችን አፍርቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X