ኒጀር ዜጎቿ እየገጠማቸው ያለውን መስተጓጎል ተከትሎ በአውሮፓውያን ላይ የቪዛ ገደብ ጣለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኒጀር ዜጎቿ እየገጠማቸው ያለውን መስተጓጎል ተከትሎ በአውሮፓውያን ላይ የቪዛ ገደብ ጣለች
ኒጀር ዜጎቿ እየገጠማቸው ያለውን መስተጓጎል ተከትሎ በአውሮፓውያን ላይ የቪዛ ገደብ ጣለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.08.2025
ሰብስክራይብ

ኒጀር ዜጎቿ እየገጠማቸው ያለውን መስተጓጎል ተከትሎ በአውሮፓውያን ላይ የቪዛ ገደብ ጣለች

የኒጀር ዜጎች በአውሮፓ ሀገራት ኤምባሲዎች ቪዛ ለማግኘት ለሚደርስባቸው ውጣ ውረድ በሰጠችው አፀፋዊ ምላሽ የአውሮፓ ዜጎች የሀገሪቱን ቪዛ ማግኘት የሚችሉባቸው ቦታዎችን ገድባለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባካሪ ያኡ ሳንጋሬ "ከዚህ በኋላ የጣሊያን፣ የኔዘርላንድ፣ የጀርመን፣ የቤልጂየም እና የዩናይትድ ኪንግደም ሀገራት ዜጎች ወደ ኒጀር ለመግባት ቪዛ ማግኘት የሚችሉት በጄኔቫ፣ አንካራ እና ሞስኮ በሚገኙ የኒጀር ኤምባሲዎች ብቻ ነው" ብለዋል።

ሳንጋሬ አክለውም ዲፕሎማቶች እና የአገልግሎት ፓስፖርት የያዙ ግለሰቦች በብራሰልስ ከሚገኘው የኒጀር ኤምባሲ ቪዛ ማግኘት እንደሚችሉ ገልፀዋል።

ውሳኔው ኒጀር ዜጎቼ የአውሮፓ ቪዛ ለማግኘት ወደ ጎረቤት ሀገራት ለምን መጓዝ ይጠበቅባቸዋል በማለት ቅሬታ ማቅረቧን ተከትሎ የመጣ ነው። የአውሮፓ ህብረት ኤምባሲዎች በኒያሜ ባሉ ቢሮዎቻቸው ውስጥ ቪዛ እንዲሰጡ የቀረበው ጥያቄም መልስ ሳያገኝ እንደቀረ ተገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0