የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣናን የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ቡድኖች ፋይናንስ ትርክት መቀየር እንደሚገባ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣናን የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ቡድኖች ፋይናንስ ትርክት መቀየር እንደሚገባ ተገለፀ
የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣናን የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ቡድኖች ፋይናንስ ትርክት መቀየር እንደሚገባ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.08.2025
ሰብስክራይብ

የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣናን የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ቡድኖች ፋይናንስ ትርክት መቀየር እንደሚገባ ተገለፀ

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የፀረ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን 25ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ስብሰባው ሀገራት ከሕግ ውጪ የሆኑ የገንዘብ እና የሽብር እንቅስቃሴዎችን በመተባበር በሚመክቱበት መንገድ ዙሪያ መክሯል።

የኢትዮጵያ የፀረ ሕገ-ወጥ ገንዘብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ እንቅስቃሴውን ለመከላከል በቡድኑ ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር ሊኖር ይገባል ሲሉ በስብሰባው ወቅት ተናግረዋል።

🟠 በአህጉሪቱ ሽብርተኝነትን ፋይናንስ ማድረግ እንዲቀር አሠራሮችን ለማዘመን እንዲሁም አባል ሀገራት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና የቴክኒክ ልህቀትን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው አመላክተዋል።

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የፀረ-ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ዋና ፀሃፊ ፊኬሊ ፒ. ዚታ በበኩላቸው ተግዳሮቱን በመቅርፍ በቀጣናው ላይ የተቀረፀው አሉታዊ ገፅታ መቀየር እንዳለበት አሳስበዋል።

ቡድኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ 21 አባል ሀገራት ያሉት እና ዋና መሥሪያ ቤቱን ታንዛኒያ ዳሬሰላም ያደረገ ክልላዊ ድርጅት ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0