ኡጋንዳ በቅርቡ ከአዲስ የነዳጅ ማውጫ ሥፍራ ነዳጅ ማምረት እንደምትጀምር አስታወቀች
18:17 27.08.2025 (የተሻሻለ: 18:24 27.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኡጋንዳ በቅርቡ ከአዲስ የነዳጅ ማውጫ ሥፍራ ነዳጅ ማምረት እንደምትጀምር አስታወቀች
በሀገሪቱ የሚገኘው የኪንግፊሸር የነዳጅ ፕሮጀክት ከተያዘለት የጊዜ ገደብ አስቀድሞ 95 በመቶ ሥራው ተጠናቋል።
የፕሮጀክቱ የሥራ ኃላፊ ክኖክ ኡጋንዳ እንደገለጸው 15 የነዳጅ ጉድጓዶች ለማምረት ዝግጁ ሆነዋል።
የቻይናው ኩባንያ የኡጋንዳ መንግሥት ፈቃድ እንዳገኘ ወዲያውኑ ማምረት ለመጀመር ዝግጁ እንደሆነና ፍቃዱም በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርቶች ጠቁመዋል፡፡
ቦታው በቀን 40 ሺህ በርሜል አካባቢ የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡ ነዳጁም ወደ ታንዛኒያ ሊጓጓዝ ይችላል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X