አፄ ኃይለ ሥላሴ የተከበረች እና የታፈረች ሀገር የምትገነባው በጥበብ እና በዕውቀት መሆኑን በሚገባ የተገነዘቡ መሪ ነበሩ - አንጋፋው ጋዜጠኛ

ሰብስክራይብ

አፄ ኃይለ ሥላሴ የተከበረች እና የታፈረች ሀገር የምትገነባው በጥበብ እና በዕውቀት መሆኑን በሚገባ የተገነዘቡ መሪ ነበሩ - አንጋፋው ጋዜጠኛ

ዛሬ ታስቦ የሚውለውን የንጉሱን ህልፈተ ህይወት 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ የነበራቸው ጋዜጠኛ እና የታሪክ አዋቂው ጥበቡ በለጠ፤ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሀገራቸውን በሥልጣኔ ከፍ ለማድረግ እና ተደማጭነቷን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወናቸውን አውስተዋል።

"ጃንሆይ ከሩሲያ እስከ ፈረንሳይ ድረስ ያሉትን አውራ ታሪኮች እያወቁ ያደጉ ናቸው። ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ሥልጣኔዎችን አይተዋል። በአንጻሩም አፍሪካ በባርነት ይደርስባት የነበረውን ግፍ ስለሚያውቁ፤ ሀገራቸውን ከፍ ለማድረግ ለጥበብ፣ ዕውቀት እና ትምህርት ልዩ ትኩረት ይሰጡ ነበር" ብለዋል።

◻ ጋዜጠኛው ኢትዮጵያ በንጉሱ ጊዜ በተለይም በጥቁር ሕዝቦች ዘንድ የነበራትን ሥፍራም አስታውሰዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0