ሩሲያ በማሊ፣ ሊቢያ፣ ቻድ እና ጋና በ2026 አዲስ የባሕል ማዕከሎችን ልትከፍት ነው
17:04 27.08.2025 (የተሻሻለ: 17:54 27.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ በማሊ፣ ሊቢያ፣ ቻድ እና ጋና በ2026 አዲስ የባሕል ማዕከሎችን ልትከፍት ነው
የሩሲያ-አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ኔትወርክ (ራፉ)፤ በአፍሪካ ሀገራት የሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች በጣም ተወዳጅ እየሆኑ መምጣታቸውን፤ የሩሲያ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ናታሊያ ክራሶቭስካያ በራፉ አባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
አክለውም በቅድመ ዝግጅት ፕሮግራሞች እና የቋንቋ ትምህርቶች ዘንድሮ በደርዘን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች በተለይም በእርሻ፣ በቴክኒክ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መቀላቀላቸውን ጠቁመዋል።
የሕዝብ ዲፕሎማሲ ማዕከሉ አድማሱን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚያሰፋም ገልጿል፤ ከእነዚህም መካከል፦
🟠 በጥቅምት ወር በቡርኪና ፋሶ የሚጀመረው የዓለም አቀፍ የክፍል ፕሮግራም (ከቶምስክ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ እና ከሮሳቶም ጋር በመተባበር)፣
🟠 ተማሪዎችን ለሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ለማብቃት እና ለአስተማሪዎች ሥልጠና ለመስጠት ከጋና የቴክኒክ ኮሌጅ ጋር የተፈጠረው አጋርነት (ከኖቮሲቢርስክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ከኖቮሲቢርስክ ስቴት ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር) ለአብነት ተጠቅሰዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X